በዋልድባ ገዳም ከ4 በላይ ፌደራል ፖሊሶች በጅብ ተበሉ

 ( አንድ አድርገን ሚያዚያ 23 2004ዓ.ም)፡-በዋልድባ ገዳም በጥበቃ ላይ የሚገኙ ከ4 በላይ ፌደራል ፖሊሶች በጅብ ተበልተዋል ፤ ይህ ሶስተኛው ምልክት እንጂ የመጨረሻ አይደለም ፤ ይህ ጉዳይ ቦታው ላይ የሚገኙትን ፌደራል ፖሊሶች ጭንቀት ላይ ጥሏቸዋል ፤ ከፍተኛ ውጥረትም ነግሷል ፤ ቀጥሎ ማን እንደሚጎተት ስላላወቁ በሁኔታው እንቅልፍ አልወስድ ያላቸው ፌደራል ፖሊሶች በዝተዋል ፤ ለዚህ ሁሉ ነገር ተጠያቂ ግን መንግስት ነው ፤ አምላካችን ታጋሽ ነው ፤ ‹‹እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት፥ እስከ ሺህ ትውልድም ቸርነትን የሚጠብቅ፥ አበሳንና መተላለፍን ኃጢአትንም ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችንም ኃጢአት በልጆች እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድም በልጅ ልጆች የሚያመጣ አምላክ›› ኦሪት ዘጸአት 346 የምትሰሩት ስራ ከእርሱ የተደበቀ ሆኖ አይደለም ፤ ትንቢተ ኤርምያስ 17፤10 ላይ ‹‹እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ ኵላሊትንም እፈትናለሁ።›› ተብሎ ተጽፏል አንዳች ከእርሱ የሚደበቅ ስራ የላችሁም ፤ አሁንም ከስራችሁ ተመለሱ ፤ በተጨማሪ የዮሐንስ ራእይ 2፤23 ላይ ‹‹ኩላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፥ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።›› ይላል ፡፡ ባለፈው 6 ሰዎች ተፈንግለው ሞተዋል ፤ ዛሬ ደግሞ ከ4 በላይ ፖሊሶች በጅብ ተበልተዋል ፤ ስለዚህ ከእርሱ የተደበቀ ከእርሱ የተሰወረ አንዳች ነገር የለም ፤ ዛሬ ላይ ልባችሁ አብጦ ጉልበትን መከታ በማድረግ የሚሰራ ስራ ውጤቱን እያያችሁት ነው፤ ከታሪክም ተወቃሽነትም ወደ የትም አያሸሽም ፤ በሰራችሁት ስራ ይመዝናችኋል ዋጋችሁንም ይሰጣችኋል፤

‹‹የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች። ትንቢተ ኤርምያስ 31 ፤15 ፤ አሁንም አባቶች ስለምታደርጉት ነገር እያለቀሱባችሁ መሆኑን እወቁ ፤ እንባቸው ጎርፍ ሆኖም እንዳይጠራርጋችሁ ለራሳችሁ ስጉ ፤ አምላካችን የራሄልን እንባ ከአይኗ የዳበሰ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው ፡፡‹‹ የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው። ›› መዝሙረ ዳዊት 46 ፤7 ባለፈው የ9 ወር ሪፖርት ሲቀርብ የስኳር ሚኒስትሩ ስለ ዋልድባ ጥያቄ ተጠይቀው ‹‹ከእውነት የራቀ ነው ይህ ዋሺንግተን ላይ የተወራ ወሬ ነው›› በማለት መልስ ሰጥተው ነበር፡፡በትንቢተ ኢሳያስ 1፤24 ላይ ‹‹የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፥ እርሱም ይዋረዳል›› ይላል ሀይል የእግዚአብሔር መሆኑን እናምናለን ፤ ነገር ግን ስጋውያን ትላንት ታይተው ከደቂቃዎች በኋላ እንደ ጤዛ ለሚደርቁ ጉልበተኞች በዘመናችን ቢያጋጥሙን ለሰው ልጅ ጉልበት የሚሆን ጉልበትንም የሚሰብር እርሱ አምላካችን እግዚአብሔር እንደሆነ በዚህ ይወቁ፡፡ ‹እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ›› ኦሪት ዘጸአት 1414 ፤ ይህን የዋልድባ የስኳር ልማት መቃወም እና ከእኩይ አላማቸው መግታት ቢያቅተን መጽሀፍ ቅዱስ ‹ተሰለፉ፥ ዝም ብላችሁ ቁሙ፥ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን መድኃኒት እዩ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ነውና አትፍሩ፥ አትደንግጡም፥›› መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 20 ፤17 ይላል ፤ እኛ ዝም እንላለን የእሱንም ስራ እያየን መከራችሁን እየቆጠርን እንቀመጣለን ፤ አሁን ሶስት ብለናል ፤ ነገ ሰላሳ እንደምንል አንጠራጠርም ፤ ካልተመለሳችሁ ቁጣው ይብሳል ፤ ሰይፉም ይሰላል ፡፡

ባለፈው ቀጣዩን ለማቅረብ ቃል ገብተን ነበር ፤ አሁንም ቀጣዩን ተዓምር ለማቅረብ ቃል እገባለን

ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበበብ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ
Advertisements

Posted on April 30, 2012, in ዋልድባ. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: