Category Archives: ወቅታዊ ጉዳይ

የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ካህናት፣ ሰበካ ጉባኤና ሰንበት ት/ቤት በ”ችግር ፈጣሪው” አስተዳዳሪ አባ ሚካኤል ታደሰ ታውከዋል

  • በአስተዳዳሪነት የተሾሙት ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንና ቃለ ዐዋዲውን በመጣስ ለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች ተገዥ ባለመኾናቸው ማዕርገ ክህነታቸው ተሽሮ በሥልጣነ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ከተወገዙ በኋላ ነው።
·         ሀ/ስብከቱ የሀብት ቁጥጥርን ለማጠናከር ያስተላለፈውን መመሪያ በመጣስ ዘረፋን ያበረታታሉ።
·        ሰንበት ት/ቤቱን ‹ማኅበረ ቅዱሳን ናቸው› በሚል አገልግሎቱን የሚያደናቅፉ ርምጃዎች ወስደዋል።
·        አስተዳዳሪው ከአባ ጳውሎስ የኤጲስ ቆጶስ ሢመት ተስፈኞች አንዱ ናቸው።
 
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 8/2004 ዓ.ም፤ ጁን 15/ 2012/) በማዕርገ ዲቁናቸው በእቲሳ ደብረ ጽላልሽ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም በዐቃቢነት አገልግለዋል፡፡ ያን ጊዜ ስማቸው ዲያቆን ሙሉነህ ታደሰ ይባል ነበር፡፡ በገዳሙ ማዕርገ ምንኵስና ሲቀበሉ ስማቸው አባ ኀይለ ኢየሱስ ታደሰ መባሉን የገዳሙ አስተዳደር በቁጥር 79/05/98 በቀን 16/05/1998 ዓ.ም የሰሜን ኦሞ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የግለሰቡን ማንነት አስመልክቶ ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ የሰጠበት ደብዳቤ ያስረዳል፡፡ Read the rest of this entry
Advertisements

ኢትዮጵያ ግብረሰዶምንና አራማጆቹ ምዕራባዊያንን አወገዘች

" ከሀይማኖት ወዲያ ምን አለ፣ ለሀይማኖት መሞት ጽድቅ ነው።" የገዳሙ አባቶች

በባቦጋያ ምስራቀ ፀሐይ ቤተክርስቲያን ለጠፈጠረዉ ዉዝግብ በፍትሐብሔር ሕግና በቃለዓዋዲዉ አኳያ ሲታይ

የአባቶቼን ርስት እሰጥህ ዘንድ እግዚአብሔር ያርቅልኝ (1ነገ20፡11)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
በባቦጋያ ምስራቀ ፀሐይ ቤተ ክርስቲን ለጠፈጠረዉ ዉዝግብ መነሻ የሆነ በደብሩ የሰበካ ጉባኤ ተወካዮችና በአቶ ታዲዎስ ጌታቸዉ መካከል የተፈረመዉ ዉል በፍትሐብሔር ሕግና በሕገመንግስቱ እንዲሁም በቃለ ዓዋዲዉ ሲታይ

1.1 በፍትሐብሔር ሕግና ሕገ መንግስት ዉሉ ሲተነተን
የባቦጋያ ምስራቃ ፀሐይ መድሃኒአለም ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ሰኔ 2/1999ዓ.ምያሳለፈዉን ዉሳኔ መሰረት ማድረግ ሰኔ 10/2004ዓ.ም በበጎ ፈቃደኝነት የተደረገ የዉል ስምምነት በሚል ርእሰ የኩሪፍቱ ሪዞርትና ስፖ ባለቤት ከሆኑት ከአቶ ታዲዎስ ጌታቸዉ ጋር ባደረጉት የመንደር ዉል የቤተ ክርስትያንቱን የመስቀልና የጥምቀት በዓላት ማክበሪያ የነበረዉን 13,020 ካሬ ሜትር ስፋት ያለዉን ፤ በስተ ደቡብ ከኩሪፍቱ ሐይቅ ጋር የሚዋሰነዉን ቦታ እንድታጣ አድርጓታል፡፡ይኼ በወቅቱ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ አስተዳደርና በአቶ ታዲዎስ ጌታቸዉ መካከል የተደረገዉ ስምምነት ከኢትዮጵያ የፍትሐብሔርና ሕገመንግስት ሕግ ማእቀፍ ዉጭ የሆነ፣የስምምነቱ ርእሰ ጉዳይ ወይም የዉለታዉ ጉዳይ (object of the contract) ተለይቶ የማይታወቅ እና ይልቁንም በዉስጡ የተገለፀዉን ለአቶ ታዲዎስ የቤተ ክርስቲያንቱን መሬት በነጻ የመስጠትን ዓላማ ማረጋገጥ የማይቻል ሲሆን በአንፃሩ ቤተ ክርስቲያንቱ ሐይማኖታዊና ብሔራዊ በዓላቶቿን የምታከብርባቸዉን ቦታዎች ያለ አንዳች ጥቅም እንድታጣ ያደረገ እና የቢሾፍቱ ከተማን ማዘጋጀ ቤት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በቸልተኝነትም ይሁን ሆን ተብሎ ሕገ-ወጥ እና ኢ-ፍትሐዊ የሆነና የሚያስወቅስ ድርጊት እንዲፈፅም ምክንያት የሆነ ስምምነት ነዉ፡፡ Read the rest of this entry

‹‹ቤተክርስትያኒቱ አትዘጋም›› ያሉ 16 ክርስትያኖች ታሰሩ

ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበበብ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ 

http://www.andadirgen.blogspot.in

https://andadirgen1.wordpress.com

(አንድ አድርገን ሚያዚያ 19 ፤ 2004ዓ.ም)፡– የባቦጋያ መድሀኒአለም ቤተክርስትያን የቦታ ጉዳይ ለያዥ ለገናዥ እያስቸገረ ይገኛል ፤ አቶ ጌታቸው ዶኒ እንዳሰበው ነገሮች እየሄዱ አለመሆናቸውን ሲረዳ የቤተክርስትያኒቱን ቄሰ ገበዝ ትላንት አመሻሽ ላይ የመቅደሱን ቁልፍ ካለመጡ ብሎ ጠይቋቸው ነበር ፤ እርሳቸውም ‹‹አንተ ማነህና ነው የቤተክርስትያኒቱን ቁልፍ የምሰጥ ›› በማለት እምቢ ሲሉት ጉልበት ተጠቅሞ ቁልፉን እጁ ለማስገባት ሙከራ አድርጎ  ነበር ፤ ቄሰ ገበዙ የመቅደሱን ቁልፍ አልሰጥም በማለት ለአካባቢው ክርስትያኖች ስልክ ደውለው በአጭር ጊዜ ውስጥ ክርስትያኖቹ የተሰበሰቡ ሲሆኑ ከደቂቃዎች በኋላ ጌታቸው ‹‹አመጽ ለማስነሳት ሰዎች ተሰብስበዋል›› ብሎ በደወለላቸው ፖሊሶች አማካኝነት በጊዜው የነበሩትን 16 ክርስትኖችን  እስር ቤት ሊያስገቧቸው ችለዋል ፡፡ ከእነዚህ ውስጥም ሶቶች ጎልማሶችና ፤ ወጣቶች ይገኙበታል ፤  የእነዚህ ንጹሀን ክርስትያኖች  ተቃውሞ ‹‹አቶ ጌታቸው ዶኒ  የቤተክርስትያኒቱን ቁልፍ ለምን ይቀበላል ? ቁልፉን ተቀብሎ ከዚህ በፊት ሲናገር እንደነበረው የባቦጋያን መድሀኒአለም ቤተክርስትያን ለመዝጋት የሚያደርገውን ተግባር እንቃወማለን ፤ ›› በማለታቸው ነው ለእስር የበቁት፡፡ Read the rest of this entry

ዋልድባ አወዛጋቢነቱ እንደቀጠለ ነው

  •  ማኅበረ ቅዱሳን በዋልድባ ጉዳይ ከፓትርያሪኩ እና ከመንግሥት ጋራ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።
  •  ማኅበሩ የወልቃይት ስኳር ፕሮጀክት በዋልድባ ገዳም ላይ ስለሚያደርሰው ተጽዕኖ ያጠናቀረውን ሪፖርት አስመልክቶ መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል::
  •  “እስከ 20 ሄ/ር የገዳሙ መሬት በግድቡ ውኃ ይሸፈናል፤ ፕሮጀክቱ የገዳሙን 40% የምርት ገቢ 60% የምእመናን ድጋፍ ያሳጣዋል” (የማኅበሩ አጥኚ ቡድን ሪፖርት)::
  •  ማኅበሩ የፕሮጀክቱ አካባቢ ከሚለወጥበት እስከ ዲዛየን ማሻሻያ የሚደርስ የጥናት አማራጭ እንዲያቀርብ፣ ገዳማውያኑ ስለ ፕሮጀክቱ ማኅበራዊ እና አካባቢያዊ ተጽዕኖ ያላቸው ሐሳብ የሚደመጥበት አቋማቸውንም ያለጫና የሚያሳውቁበት መድረክ እንዲያመቻች ተጠይቋል::
  •  የስኳር ኮርፖሬሽኑ በፕሮጀክትና ፋብሪካ ማኔጅመንት የአቅም ማነስ ችግር እንዳጋጠመው አስታውቋል::
  •  “ወደ ፕሮጀክቱ ትግበራ ከመግባታችን አስቀድሞ መነኰሳቱን እንደ መንግሥት በአለማነጋገራችን አጥፍተናል፤ እነርሱን [የቤተ ሚናስ ማኅበረ መነኰሳትን] ማማከር ነበረብን፡፡” (የፕሮጀክቱ ሓላፊዎችና የወረዳው ባለሥልጣናት)::
  •  “መንግሥት የፕሮጀክቱን የጥናት ሰነዶች ይፋ ያድርግ” (አንድ የኢንቫይሮመንታል ዲዛይን ምሁር)::

(ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 19/2004 ዓ.ም፤ April 27/2012)፦ መንግሥት በክልል ትግራይ ምዕራባዊ ዞን ወልቃይት ወረዳ በሚገኘው የዛሬማ፣ ዱቁቆ እና ተከዜ ሸለቆ በሚያካሂደው የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት የተነሣ ከአገራችን ታላላቅና ቀደምት ቅዱሳት መካናት አንዱ በኾነው በዋልድባ ገዳም ህልውናና ክብር ላይ የተጋረጠው አደጋ ለብዙኀን መገናኛ ዘገባ ከዋለ ድፍን ሁለት ወራት ተቆጥረዋል፡፡ Read the rest of this entry

አቶ ጌታቸው ዶኒ በሰላም አልሳካ ሲለው ጉልበት እየተጠቀመ ይገኛል