Category Archives: ዋልድባ

በዋልድባ ጉዳይ ከ20 በላይ ወጣቶች ታስረዋል

የዋልድባን ገዳም እናድን የሚሉ ሰላማዊ ሰልፎች በዓለም ዙርያ ሲካሄዱ ውለዋል

በዋልድባ ከሶስት ሺህ ሰው በላይ ለተቃውሞ መንግስት ላይ ተነሳስቷል

አባቶች ስለ ዋልድባ ዝምታን ለምን መረጡ ?

የዋልድባ ገዳም ጉዳይ እንደ አጀንዳ አለመያዙ እያነጋገረ ይገኛል

በዋልድባ ገዳም ከ4 በላይ ፌደራል ፖሊሶች በጅብ ተበሉ

 ( አንድ አድርገን ሚያዚያ 23 2004ዓ.ም)፡-በዋልድባ ገዳም በጥበቃ ላይ የሚገኙ ከ4 በላይ ፌደራል ፖሊሶች በጅብ ተበልተዋል ፤ ይህ ሶስተኛው ምልክት እንጂ የመጨረሻ አይደለም ፤ ይህ ጉዳይ ቦታው ላይ የሚገኙትን ፌደራል ፖሊሶች ጭንቀት ላይ ጥሏቸዋል ፤ ከፍተኛ ውጥረትም ነግሷል ፤ ቀጥሎ ማን እንደሚጎተት ስላላወቁ በሁኔታው እንቅልፍ አልወስድ ያላቸው ፌደራል ፖሊሶች በዝተዋል ፤ ለዚህ ሁሉ ነገር ተጠያቂ ግን መንግስት ነው ፤ አምላካችን ታጋሽ ነው ፤ ‹‹እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት፥ እስከ ሺህ ትውልድም ቸርነትን የሚጠብቅ፥ አበሳንና መተላለፍን ኃጢአትንም ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችንም ኃጢአት በልጆች እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድም በልጅ ልጆች የሚያመጣ አምላክ›› ኦሪት ዘጸአት 346 የምትሰሩት ስራ ከእርሱ የተደበቀ ሆኖ አይደለም ፤ ትንቢተ ኤርምያስ 17፤10 ላይ ‹‹እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ ኵላሊትንም እፈትናለሁ።›› ተብሎ ተጽፏል አንዳች ከእርሱ የሚደበቅ ስራ የላችሁም ፤ አሁንም ከስራችሁ ተመለሱ ፤ በተጨማሪ የዮሐንስ ራእይ 2፤23 ላይ ‹‹ኩላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፥ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።›› ይላል ፡፡ ባለፈው 6 ሰዎች ተፈንግለው ሞተዋል ፤ ዛሬ ደግሞ ከ4 በላይ ፖሊሶች በጅብ ተበልተዋል ፤ ስለዚህ ከእርሱ የተደበቀ ከእርሱ የተሰወረ አንዳች ነገር የለም ፤ ዛሬ ላይ ልባችሁ አብጦ ጉልበትን መከታ በማድረግ የሚሰራ ስራ ውጤቱን እያያችሁት ነው፤ ከታሪክም ተወቃሽነትም ወደ የትም አያሸሽም ፤ በሰራችሁት ስራ ይመዝናችኋል ዋጋችሁንም ይሰጣችኋል፤ (more…)

ዋልድባ አወዛጋቢነቱ እንደቀጠለ ነው

  •  ማኅበረ ቅዱሳን በዋልድባ ጉዳይ ከፓትርያሪኩ እና ከመንግሥት ጋራ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።
  •  ማኅበሩ የወልቃይት ስኳር ፕሮጀክት በዋልድባ ገዳም ላይ ስለሚያደርሰው ተጽዕኖ ያጠናቀረውን ሪፖርት አስመልክቶ መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል::
  •  “እስከ 20 ሄ/ር የገዳሙ መሬት በግድቡ ውኃ ይሸፈናል፤ ፕሮጀክቱ የገዳሙን 40% የምርት ገቢ 60% የምእመናን ድጋፍ ያሳጣዋል” (የማኅበሩ አጥኚ ቡድን ሪፖርት)::
  •  ማኅበሩ የፕሮጀክቱ አካባቢ ከሚለወጥበት እስከ ዲዛየን ማሻሻያ የሚደርስ የጥናት አማራጭ እንዲያቀርብ፣ ገዳማውያኑ ስለ ፕሮጀክቱ ማኅበራዊ እና አካባቢያዊ ተጽዕኖ ያላቸው ሐሳብ የሚደመጥበት አቋማቸውንም ያለጫና የሚያሳውቁበት መድረክ እንዲያመቻች ተጠይቋል::
  •  የስኳር ኮርፖሬሽኑ በፕሮጀክትና ፋብሪካ ማኔጅመንት የአቅም ማነስ ችግር እንዳጋጠመው አስታውቋል::
  •  “ወደ ፕሮጀክቱ ትግበራ ከመግባታችን አስቀድሞ መነኰሳቱን እንደ መንግሥት በአለማነጋገራችን አጥፍተናል፤ እነርሱን [የቤተ ሚናስ ማኅበረ መነኰሳትን] ማማከር ነበረብን፡፡” (የፕሮጀክቱ ሓላፊዎችና የወረዳው ባለሥልጣናት)::
  •  “መንግሥት የፕሮጀክቱን የጥናት ሰነዶች ይፋ ያድርግ” (አንድ የኢንቫይሮመንታል ዲዛይን ምሁር)::

(ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 19/2004 ዓ.ም፤ April 27/2012)፦ መንግሥት በክልል ትግራይ ምዕራባዊ ዞን ወልቃይት ወረዳ በሚገኘው የዛሬማ፣ ዱቁቆ እና ተከዜ ሸለቆ በሚያካሂደው የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት የተነሣ ከአገራችን ታላላቅና ቀደምት ቅዱሳት መካናት አንዱ በኾነው በዋልድባ ገዳም ህልውናና ክብር ላይ የተጋረጠው አደጋ ለብዙኀን መገናኛ ዘገባ ከዋለ ድፍን ሁለት ወራት ተቆጥረዋል፡፡ Read the rest of this entry

በዋልድባ መንግስት ሬሳ መልቀምን ተያይዞታል

በዋልድባ የመጀመሪያው ምልክት

የዋልድባ ጉዳይ